Matthew 4:20
TSK
ወዲያውም መረባቸውን ትተው ተከተሉት።
TSK
Treasury of Scripture Knowledge references in መጽሐፍ ቅዱስ.
ወዲያውም መረባቸውን ትተው ተከተሉት።
በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ መልሶ። እነሆ፥ እኛ ሁሉን ትተን ተከተልንህ፤ እንኪያስ ምን እናገኝ ይሆን? አለው።
ኢየሱስም ወደ እርሱ ተመልክቶ ወደደውና። አንድ ነገር ጐደለህ፤ ሂድ፥ ያለህን ሁሉ ሽጠህ ለድሆች ስጥ፥ በሰማይም መዝገብ ታገኛለህ፥ መስቀሉንም ተሸክመህ ና፥ ተከተለኝ አለው።
ሁሉንም ተወ፤ ተነሥቶም ተከተለው።
ነገር ግን ለእኔ ረብ የነበረውን ሁሉ ስለ ክርስቶስ እንደ ጉዳት ቈጥሬዋለሁ።